ስለኛ

ራዕይ

    በ2017 ዓ.ም. የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ የህዝብ አመኔታ ያተረፈ ተቋም ሆና ማየት

ተልዕኮ

በአዲስ አበባ ከተማ የተቀላጠፈ የፍትህ አገልግሎት በነጻነት፣ በገለልተኛነትና ህግን መሰረት በማድረግ ለህብረተሰቡ በመስጠት የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ማድረግ፡፡


ስልጣን፣ ተግባርና ኃላፊነት

  • የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች በተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/95 መሰረት የተቋቋሙ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዳኝነት አካል ናቸው፡፡
    • ፍርድ ቤቶቹ በመጀመሪያ እና በይግባኝ ሰሚነት ደረጃ የተዋቀሩ ሲሆን የመጀመርያ ደረጃ ፍ/ቤቱ በከተማው ፍ/ቤቶች የዳኝነት ሥልጣን ስር በሚወድቁ ጉዳዮች ላይ የመጀመርያ ደረጃ የዳኝነት ሥልጣን ሲኖረው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ ደግሞ በከተማው የመጀመርያ ደረጃ ፍ/ቤት እና የመዳኘት ስልጣን በተሰጣቸው ሌሎች አካላት የሚሰጡ ውሳኔዎች ላይ የይግባኝ ሰሚነት ስልጣን አለው፡፡
      • ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤቱ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ሲሆን ነገር ግን ፍ/ቤቱ የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት የሚል ወገን የሰበር ቅሬታውን በአዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ስር ለተቋቋመው ሰበር ሰሚ ችሎት ማቅረብ ይችላል፡፡
        • ፍርድ ቤቶቹ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 41፤ በቻርተሩ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 408/98 እንዲሁም በፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234 ላይ በተዘረዘሩት ጉዳዮች ላይ አከራክሮ ውሳኔ የመስጠት የዳኝነት ስልጣናቸው እንደተጠበቀ ሆኖ የማህበራዊ ፍርድ ቤቶች፣ የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን እንዲሁም የከተማው የመንግስት ሰራተኞች አስተዳደር ፍርድ ቤት በሚሰጧቸው ውሳኔዎች ላይ የይግባኝ ሰሚነት ስልጣን አላቸው፡፡
          • በአዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀፅ 41፤ በቻርተሩ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 408/98 መሰረት እንዲሁም በፌዴራል ፍርድ ፍ/ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234 አንቀጽ 5(1) (ደ) እና አንቀጽ 4(16) መሰረት የሚከተሉት ጉዳዮችን አከራክሮ ውሳኔ የመስጠት የዳኝነት ስልጣን አለቸው፡-
            • በአዋጅ 361/95 ዓ.ም እና 408/01 የተሰጠን ስልጣን መተርጎም
              • ስልጣንና ተግባራት የስልጣን ምንጭ የመንግስት ስልጣን በህግ ከተቀመጠለት ገደብ እንዳያልፍና ይህንንም በተግባር ለማረጋገጥ መጀመሪያ የስልጣንን ምንጭ እና መገለጫ ባህርያት በቅጡ መረዳት ያስፈልጋል

እሴቶች

  • የላቀ አገልግሎት እንሰጣለን፣
    • ነፃነትና ተጠያቂነት
      • ግልጽነት፣
        • ለፍትህና ለሕግ የበላይነት በፅናት እንታገላለን
          • ቅን አገልጋይ መሆን
            • ከሙሱና የጸዳ አገልግሎት መስጠት
              • ቀልጣፋ ዘመናዉ የመረጃ አያያዝ መዝጋት

መልዕክቶች

የወንጀል ወይም የደንብ መተላለፍ የዳኝነት ስልጣን፡-

 በአዋጁ አንቀፅ 52 በተመለከቱ የፋይናንስ ጉዳዮች ላይ የሚነሱ የወንጀል ጉዳዮች፣  የደንብ መተላለፍ ጉዳዮች፣  በግል አቤቱታ አቅራቢነት የሚያስከስሱ የወንጀል ጉዳዮችን፤  በፌደራል ወንጀሎች ላይ የፌደራል ፍርድ ቤቶች ስልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ በ1954 ዓ.ም. የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ስርአት ህግ አንቀጽ 33፤35፤53 እና አንቀጽ 59 መሰረት የብርበራ ትእዛዝ መስጠት ፤እምነት ቃልን የመመዝገብ፣የመያዣ ትዕዛዝ መስጠት እንዲሁም ዋስትናን ወይም ማረፊያ ቤት ማቆየትን በተመለከተ የሚቀርቡ ጉዳዮችን መርምሮ ትእዛዝ የመስጠት፣  በከተማው አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት የሚጣሉ የደንብ መተላለፍ ቅጣቶችን የማስፈፀም ጉዳዮች ላይ ስልጣን አላቸው፡

የፍትሐ-ብሄር የዳኝነት ስልጣን

የከተማውን መሪ ፕላን አፈፃፀም የሚመለከት የይዞታ ባለመብትነት፣ የፍቃድ አሰጣጥ ወይም የቦታ አጠቃቀምን በተመለከተ የሚነሱ ጉዳዮች፣

የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት እሴቶች

ለለውጥ ዝግጁ ነን፣

ማስታወቂያዎች

ሰነዶች፣ ደንቦችና መመሪያዎች፣ እቅዶችና ሪፖርቶች

    Proc No. 408-2004 Addis Ababa City Government Revised Chart  Proc No. 408-2004 Addis Ababa City Government Revised Chart
ተጨማሪ
    Proc No. 361-2003 Addis Ababa City Government Revised  Proc No. 361-2003 Addis Ababa City Government Revised Charter
ተጨማሪ

ችሎቶች

አድራሻችን