ለአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች ዳኞች ስልጠና መስጠት ተጀመረ::

ወቅቱ የሚጠይቀውን የዳኝነት ሥርዓት ለመፍጠር የዳኞችን አቅም ማጎልበት እንደሚገባ ተገለጸ:: የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች የዳኞች መደበኛ የሥራ ላይ ሥልጠና መሰጠት ተጀምሯል። የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች ከፌዴራል የፍትሕ፣ የሕግ ምርምር እና ሥልጠና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የተዘጋጀው የዳኞች ሥልጠና ለ10 ቀናት የሚቆይ ነው። በዐሥሩ ቀናት የሥልጠና ቀናትም የኢትዮጵያ የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር እና የፀረ ሽብርተኝነት ሕግ፣ የአዲስ አበባ እና የፌዴራል የመንግሥት ቤቶች አስተዳደር መመሪያ፣ የዳኝነት ሥነ ምግባር፣ የጉዳዮች ፍሰት እና የችሎት አመራር እንዲሁም የጊዜ ቀጠሮና የዋስትና አሰጣጥ ላይ ዳኞቹ ስልጠና ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።